Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ በተገኘ 100 ሚሊየን ብር ቤተ መጻሕፍት ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ከተማ ከመደመር ትውልድ መፅሐፍ ሽያጭ በተገኘ 100 ሚሊየን ብር ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍት ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጧል፡፡ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በወቅቱ እንዳሉት÷ የምንፈልጋትንና የበለፀገችውን ኢትዮጵያን…

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ለ630 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የ2016 ዓም አዲስ ዓመት በማስመልከት ለ630 የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ ። የክልሉ መንግስት በሰባት ማረሚያ ቤቶች በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ውሳኔ አግኝተው የፍርድ ጊዜያቸውን በመፈፀም ላይ ከሚገኙ የሕግ…

የህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ለትውልድ አሻራ ማስቀመጥ እንደሚቻል ማሳያ ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቅ ፈተናዎችን ተቋቁሞ ለትውልድ የሚሸጋገር አሻራ ማስቀመጥ እንደሚቻል ትምህርት የሰጠ መሆኑን ምሁራን ገለጹ፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 4ኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት…

11ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው የዓመቱ በጎ ሰው ሽልማት ሥነ-ስርዓት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። በሽልማት ስነ-ሥርዓቱ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ቀና እንድትል ላደረጉ እና የተለያዩ በጎ ስራዎችን ላከናወኑ በጎ ሰዎች እውቅና ተሰጥቷል። ባለፋት 10 ዓመታት…

በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል፡፡ የጸሎት መርሐ ግብሩ አዲሱን 2016 ዓመተ ምህረት በይቅርታና በእርቅ መቀበልን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡ በመርሐ ግብሩ አዲሱ…

በኒውካስል ግማሽ ማራቶን አትሌት ታምራት ቶላ አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ኒውካስል በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ታምራት ቶላ አሸንፏል፡፡ አትሌት ታምራት ቶላ ርቀቱን 59 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነው፡፡ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሙክታር እድሪስ ደግሞ…

በመልካም ስነ-ምግባር የታነጸ ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራት የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን – የሃይማኖት አባቶች

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ትውልድን በስነ-ምግባር በማነጽ ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራት የጀመርነውን ስራ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ የሃይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡ ጳጉሜን 5 የትውልድ ቀን "ኢትዮጵያ የትውልዶች ድምር" በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል።…

በጎነት ከማይነጥፍ የመልካምነት እሴት የሚቀዳ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ ፣ ጳጉሜን 3 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎነት ከማይነጥፍ የመልካምነት እሴት የሚቀዳ እንዲሁ በነጻ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጳጉሜን 3 ቀን የበጎነት ቀንን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፥ በጎነት መስፈርት የለውም…

ከ30 ቢሊየን ብር በላይ የታክስ ጉዳት አድርሷል የተባለው ተከሳሽ ማረሚያ ቤት እንዲወርድ ታዘዘ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ30 ቢሊየን ብር በላይ የታክስ ጉዳት በመንግስት ላይ አድርሷል የተባለው ተከሳሽ የዋስትና ጥያቄው ውድቅ ተደርጎ ማረሚያ ቤት እንዲወርድ ታዘዘ፡፡ ትዕዛዙን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሙስና ወንጀል ተረኛ ወንጀል ችሎት…

በአፋር ክልል የበጎነት ቀን እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የበጎነት ቀን "በጎነት ለሀገር" በሚል መሪ ሃሳብ በአፋር ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው። የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ደረሳ መሐመድ እንዳሉት÷ ቀኑን የቢሮው ሰራተኞች ከደመወዛቸው ቀንሰው ሌሎችን እገዛ…