Fana: At a Speed of Life!

በመደመር ፍልስፍና ገዥ ትርክቶችን በማጎልበት አንድነትን ማጠናከር ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመደመር ፍልስፍና ገዥ ትርክቶቻችንን በማጎልበት አንድነታችንን ልናጠናክር ይገባል ሲሉ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የጥናትና ምርምር ክፍል ሃላፊና የኮምቦልቻ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ ተተካ በቀለ ገለፁ። በኮምቦልቻ ከተማ የ4ኛው ዙር…

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

አዲስ አበባ ፣ ሕዳር 25 ፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን አስታውቋል።

ህግና ህገ መንግስቱ የተቋቋመው የህዝቦችን እኩልነት ለማረጋገጥ ነው – ም/አፈ ጉባኤ ኤሊያስ ኡመታ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ህግና ህገ መንግስቱ የተቋቋመው የህዝቦችን እኩልነት ለማረጋገጥ ነው ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ ም/አፈ ጉባኤ ኤሊያስ ኡመታ ተናገሩ፡፡ 18ኛው የብሔር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን በማስመልከት በኦሮሚያ ክልል ደረጃ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በማያ ከተማ…

አቶ አገኘሁ ተሻገር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ የፋና ብሮድካስቲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አድማሱ ዳምጠውን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ…

7ኛው ዙር የኦዳ አዋርድ ታኅሣሥ 11 ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮ ኦዳ አዋርድ ለ7ኛ ጊዜ ታኅሣሥ 11 ቀን እንደሚካሄድ አስተባባሪዎቹ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል። የኦዳ አዋርድ በዚህኛው ዙር ከሀገር አልፎ አፍሪካውያን የሚሸለሙበት መድረክ እንደሚሆንም ነው የተገለጸው። ኢትዮጵያ…

ሙስናን በአስተሳሰብና በተግባር በመፋለም ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሙስናን በአስተሳሰብና በተግባር በመፋለም የሁላችንንም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በጋራ እንስራ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ፡፡ “ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በጋራ እንታገለው” በሚል መሪ ቃል ከተማ…

የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ለማስተዋወቅ ያለመ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የበለጠ ለማስተዋወቅ ያለመ መርሐ ግብር በባሌ ሮቤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊና የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራን ጨምሮ…

መዲናችን አካታችነቷን የምታሳየው አካል ጉዳተኞችን ጭምር ተጠቃሚ በማድረግ ነው – ከንቲባ አዳነች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መዲናችን አካታችነቷና የብልፅግና ተምሳሌትነቷን የምታሳየው አካል ጉዳተኞችን ጭምር ተጠቃሚ በማድረግ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ 31 ኛውን ዓለም…

የዓለም ስራ ድርጅት አባልነት 100ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል እና የብሔራዊ የአሰሪና ሰራተኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ )"ማህበራዊ ምክክርና ምርታማነት ለማህበራዊ ፍትህ "በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ የ100ኛ ዓመት የዓለም ስራ ድርጅት አባልነት መታሰቢያ በዓል እና የብሔራዊ የአሰሪና ሰራተኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡ የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚሁ ጊዜ…

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ የቀድሞ ጠ/ሚ ቶኒ ብሌር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር ጋር ተወያይተዋል። ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ውይይቱን ያደረጉት ከኮፕ28 ጉባኤ ጎን ለጎን መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡