Fana: At a Speed of Life!

የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 3 ነጥብ 25 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ሥራ መከናወኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት 3 ነጥብ 25 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ የኮንክሪት ሙሊት ሥራ መከናወኑን የፕሮጀክቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ገለጹ። ፕሮጀክቱን በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት የፕሮጀክቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ…

የንግድ ኢ-ሜይል ጥቃቶች መከላከያ መንገዶች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ኢ-ሜይል ጥቃቶች ውስብስብና አስቸጋሪ ቢሆኑም መሰል ጥቃቶች እንዳያጋጥሙ ቀድመው የሚከላከሉባቸው መንገዶች አሉ፡፡ የንግድ ኢ-ሜይል የሳይበር ጥቃት የሳይበር አጥቂዎቹ በንግድ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩና ከድርጅቱ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ወይም…

የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ ውይይቱ የክልሉ ሕዝብ የሚያነሳውን የመልካም አሥተዳደር፣ የልማት ሥራዎች እና ሌሎች ጥያቄዎችን መመለስ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡ በውይይት…

60 በመቶ ያህሉን ክትባት በአፍሪካ ለማምረት ፕሮግራም መቀረጹ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2040 ስልሳ በመቶ የሚሆነውን ክትባት በአፍሪካ ውስጥ ለማምረት የሚያስችል ፕሮግራም መቀረጹን የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በ37ኛው የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ ፍትሐዊነት፣ ራስን መቻልና የሕዝብ ጤና ጥበቃ…

ሩሲያ የምሥራቅ ዩክሬኗን አዲቪካ ከተማ ተቆጣጠረች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ ወታደራዊ ኃይሎች በምሥራቃዊ ዩክሬን የምትገኘውን የአዲቪካ ከተማን መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል፡፡ ከተማዋ በሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር የዋለችው የአሜሪካ ወታደራዊ እርዳታ መዘግየቱን ተከትሎ ዩክሩን የተተኳሽ እጥረት ስላጋጠማት አዲቪካን ለቃ…

ኢትዮጵያ ከሞሮኮ እና አልጄሪያ ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመሥራት ተስማማች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከሞሮኮ እና አልጄሪያ ጋር በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመሥራት መግባባት ላይ መድረሷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሞሮኮ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ናስር ቡርታ ጋር ባደረጉት ውይይት÷…

በቴሌኮሙኒኬሸን፣ ቱሪዝምና ቆዳ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር መሥራት እፈልጋለሁ- ዛምቢያ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛምቢያ በቴሌኮሙኒኬሸን፣ ቱሪዝምና በቆዳ ኢንዱስትሪ መስኮች ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር መሥራት እንደሚፈልግ የሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እና ሳይንስ ሚኒስትር ፍሌሲ ሙታቲ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በቴሌኮሙኒኬሸን መሰረተ ልማት ከዛምቢያ በላቀ ደረጃ ላይ…

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስተዋወቂያ መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያስተዋውቅ መድረክ በስዊድን ተካሂዷል፡፡ በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ምሕረተአብ ሙሉጌታ÷ ስለኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለኢኮኖሚ ልማት ሂደቶችና እየተገኙ ስላሉ ውጤቶች በመድረኩ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡…

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ፣የኬፕ ቨርዴ ፕሬዚዳንት ጆሴ ማሪያ ፔሬራ ኔቬስና የጊኒ ቢሳዖ ፕሬዚዳንት ኡማሮ ሲሶኮ በ37ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል። የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በጉባዔው…

ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸው ተገለጸ፡፡ የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በኤፍኤስአር ተሽከርካሪ የተለያየ አይነት 1 ሺህ 190 የሞባል ቀፎዎች እና 4 ሺህ 996 የሞባይል ባትሪዎች ናቸው ተብሏል፡፡…