Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ከ845 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ በጀት የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል መንግስት በመደበው ከ845 ሚሊየን ብር በላይ በጀት በትግራይ ክልል አምስት ከተሞች የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን በጊዜያዊ አስተዳደሩ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ገለጸ። የምግብ ዋስትና ፕሮግራሙ በመቀሌ፣…

በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ የግብዓት ማሰባሰብ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕግና የሳይበር ሙያተኞች…

ኢትዮጵያ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን መስኮች ተሞክሮዋን አጋራች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን መስኮች ያላትን ተሞክሮ በጋና በተካሄደው 3ኛው የአፍሪካ ሚዲያ ኮንቬንሽን ላይ ማጋራቷን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡ የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኮፎ አዶ በተገኙበት በአክራ በተካሄደው 3ኛው የአፍሪካ…

የብራዚልና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በ’ዘለንስኪ የሰላም ጉባዔ’ እንደማይሳተፉ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ባዘጋጁት የሰላም ጉባዔ ላይ እንደማይሳተፉ ተነገረ። የሰላም ጉባዔው ከዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችውን…

ም/ጠ/ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮ-ቴሌኮም የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የኢትዮ-ቴሌኮም ቦርድ ሰብሳቢ ተመስገን ጥሩነህ በኢትዮ-ቴሌኮም የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎትን ጎበኙ። በጉብኝታቸውም የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ የደረሰበትን ደረጃ አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የኢትዮ-ቴሌኮም…

ወጣቱን ይዘን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እንሠራለን – አቶ እንዳሻው ጣሰው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጣቱን ኃይል ከጎናችን አሠልፈን ለኢትዮጵያ ብልጽግና እንሠራለን ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው ገለጹ፡፡ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ ከሀድያ ዞን የተለያዩ መዋቅሮች ከተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶች ጋር…

የብሪክስ ጥምረት የዲፕሎማሲ ግንኙነትን ለማስፋትና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማሳደግ ይረዳል – አምባሳደር ዲና

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የብሪክስ ጥምረት ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዕድሎችን እንድታሰፋና ኢኮኖሚያዊ ትብብሯን እንድታጠናከር ያደርጋል ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሠላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ። በኢትዮጵያ…

የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ በግብጽ ሚዲያዎች የሚነዛው የሀሰት መረጃ የዓባይን ውሃ ለብቻ የመጠቀም ራስ ወዳድነት ነው – መሀመድ አልአሩሲ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በግብጽ ሚዲያዎች የሚነዛው የሀሰት መረጃ የዓባይን ውሃ ለብቻ የመጠቀም ራስ ወዳድነት ነው ሲሉ በግድቡ ዙሪያ በዓለም አቀፍ መድረኮች በመሟገት የሚታወቁት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የውሃና ኢነርጂ…

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የጦር መሣሪዎችን ምልክት በማድረግ ወደ መረጃ ቋት ማስገባት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የጦር መሣሪያዎችን ምልክት በማድረግ ወደ መረጃ ቋት ማስገባት ጀመረ፡፡ ፌደራል ፖሊስ የጦር መሣሪያን ምልክት በማድረግ ወደ ጦር መሣሪያ መረጃ ቋት ማስገባት ላይ…

አፍሪካ ለአርቲፊሻል አስተውሎት ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት እንድትሰጥ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ትክክለኛ ድምጿን እንድታሰማ የአፍሪካ ሀገራት ለአርቲፊሻል አስተውሎት ዘርፍ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ፡፡ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስራ መሪዎችና ከመላው…