Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከ600 ኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ ግንባታ እየተከናወነ ነው-አቶ ኡሞድ ኡጁሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ከ610 ኪ.ሜ በላይ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ በመከናወን ላይ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ። እንደ ርእሰ መስተዳድሩ ገለፃ በፌዴራል መንግስት ከተጀመሩ 612 ኪ.ሜ ርዝመት ካላቸው 9 የመንገድ…

አካታችነትና ጥራት ያለው የትምህርት ሥርዓትን ለመገንባት ያለመ የፓን አፍሪካ ፓርላማ ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አካታችነት፣ ጥራትና ዘላቂነት ያለው የትምህርት ሥርዓትን ለመገንባት ያለመ 6ኛው የፓን አፍሪካ ፓርላማ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ሚድራንድ መካሄድ ተጀምሯል። ጉባኤው "አካታች፣ ጥራት ያለው፣ ተገቢ እና ዘላቂነት ያለው የትምህርት ሥርዓትን…

ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ዳኞችና ተሿሚዎች ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የስነ ምግባር ጉድለት ክስ በተመሰረተባቸው የፍርድ ቤቱ ዳኞች እና የጉባኤ ተሿሚዎች ላይ የስራ ስንብት እና የደሞዝ ቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል። ጉባኤው ባለፉት ወራት ከማህበረሰብ የቀረቡ ቅሬታዎችንና የምርመራ…

ኢትዮጵያ ከፍልሰት ጋር በተያያዘ ዘርፈ-ብዙ ተግዳሮት እየተጋፈጠች ነው – ም/ ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከፍልሰት ጋር በተያያዘ ዘርፈ-ብዙ ተግዳሮቶችን በመጋፈጥ ላይ እንደምትገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። የብሔራዊ ፍልሰት ምክር ቤት ሰብሳቢ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የምክር ቤቱን ዓመታዊ የምክክር…

አቶ ሙስጠፌ የሶማሌ ክልል የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን 47 በመቶ መድረሱን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በሶማሌ ክልል ያለው የንጹህ መጠጥ ውኃ ሽፋን ከ19 ወደ 47 በመቶ ማሣደግ መቻሉን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ አስታወቁ፡፡ ከለውጡ ወዲህ ከ15 በላይ ከተሞችን ተጠቃሚ ያደረጉ ከ300 በላይ የውኃ ጉድጓድ…

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቀሪና ድጋሚ ምርጫ ጊዜያዊ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ቀሪ እና ድጋሚ ምርጫ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ ነው፡፡ በዚህ መሰረትም በክልሉ ዳንጉር ምርጫ ክልል ለተካሄደው ምርጫ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ይፋ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡…

በቦስተን የሴቶች 10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በቦስተን በተካሄደው የሴቶች 10ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1 እሰከ 3 ደረጃ በመያዝ አሸንፈዋል፡፡ ውድድሩን መልክናት ዉዱ በ31 ደቂቃ ከ15 ሴኮንድ በመጨረስ አንደኛ ደረጃን ስትይዝ ፣ቦሰና ሙላት በ31 ደቂቃ ከ16…

በፕሪምየር ሊጉ መቻል ሲዳማ ቡናን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ28ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቻል ሲዳማ ቡናን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ማሳካት ችሏል። የመቻልን ጎሎች ከነዓን ማርክነህ ሁለት ፣ ምንይሉ ወንድሙ በፍፁም ቅጣት ምት እና አማካኙ በሃይሉ ግርማ ቀሪዎቹን…

የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ሲሰርቁ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግል ድርጅት የኮንስትራክሽን ብረታ ብረት ሲሰርቁ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል የተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ 3:30 ከጥበቃ ሰራተኞች ጋር በመተባበር…

1 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 93 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡ ከተመላሽ ዜጎቹ ውስጥ 1 ሺህ 87ቱ ወንዶች ሲሆኑ 6ቱ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል። ለተመላሽ ዜጎች…