Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2013(ኤፍ ቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለታንዛኒያ ሕዝብና መንግስት መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡ ጆን ማጉፉሊ ሌሊቱን ለህልፈት መዳረጋቸውን የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት…

አቶ ደመቀ መኮንን ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በኢትዮጵያ ከሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጀሚል አብዱላህ ጋር ተወያዩ፡፡ አቶ ደመቀ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ታሪካዊ ግንኙነት በማውሳት፣  ግንኙነትን የበለጠ ማጠናከር…

8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የጊንጪ ማከፋፈያ ጣቢያ ቅዳሜ በይፋ ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 8 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት የጊንጪ ማከፋፈያ ጣቢያ ቅዳሜ በይፋ ይመረቃል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አብርሃም በላይ የጊንጪ ባለ 230/15 የኃይል ማከፋፈያ…

የሲሚንቶና የብረት እጥረት በግንባታ ሥራዎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ገለጸ 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲሚንቶና የብረት እጥረት በግንባታ ሥራዎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑን የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ገለጸ። ሥራ ተቋራጮች ሰራተኞቻቸውን የመበተን ስጋት ውስጥ መግባታቸውንም ነው ያስታወቁት። ማህበሩ በግንባታ ኢንዱስትሪ ላይ የሚስተዋሉ…

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወቅቱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እየተዘጋጀ ነው – ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር አዲሱን የአጠቃላይ ትምህርት ስርዓተ-ትምህርት ለማሻሻልና የመጨረሻ ቅርጽ አስይዞ ወደ ተግባር ለማስገባት አውደ ጥናት እያካሄደ እንደሚገኝ ገልጿል። አውደ ጥናቱ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን በማሳተፍ…

ኦነግ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ። ለሁለት ቀናት አጠቃላይ ጉባዔውን ያካሄደው ፓርቲው አዲስ ሊቀመንበርም መርጧል። ፓርቲው ባደረገው ጉባኤ አቶ አራርሶ ቢቂላን የግንባሩ ሊቀመንበር አድርጎ…

የህዳሴ ግድቡን ማጠናቀቅ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ጭምር ነው – አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዓባይን ማልማትና የህዳሴ ግድቡን ማጠናቀቅ ለነገው ትውልድ ከመስራትም በላይ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ጭምር ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡ የህዳሴ ግድብ 10ኛ ዓመትን በማስመልከት…

በቻምፒየንስ ሊጉ ሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል፡፡ ማንቼስተር ሲቲ ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ፥ ኬቪን ደብሩይነ እና ኢካይ ጉንዶኻን የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡ በደርሶ መልስ ውጤት…

140 ዜጎች ከየመን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 140 ዜጎች በዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አማካኝነት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡ ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ለመመለስ ፍቃደኛ የሆኑትን ዜጎች ነው ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ማመቻቸቱን የገለጸው፡፡ ይህም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ…

ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ ለ80ኛ ጊዜ ደም በመለገስ ቀዳሚ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሲስተር አሰጋሽ ጎሳ ለ80ኛ ጊዜ ደም በመለገስ ቀዳሚ ሆኑ፡፡ የጤና ሚንስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በማህበራዊ ገጻቸው ይህ በኢትዮጵያ ሴት ደም ለጋሾች ዘንድ ክብረ ወሰን ነው ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ እናትም ቀዳሚ ደም ለጋሽም በመሆን በዛሬ ዕለት…