Fana: At a Speed of Life!

በወጪ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራት 21 በመቶ እድገት ተመዝግቧል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወጪ ንግድ ባለፉት ስድስት ወራት 21 በመቶ እድገት ማስመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ምላሽ የኤክስፖርት ዕድገቱ ባለፉት 20 ዓመታት ከተመዘገበው እንደሚልቅ ነው…

ምክር ቤቱ  11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚያካሂደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጀምሯል፡፡ በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች ላይ…

በድሬዳዋ በአንድ ሳምንት ውስጥ የኮቪድ 19 ምርምራ ከተደረገላቸው 380 ሰዎች ውስጥ 125ቱ ቫይረሱ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ በአንድ ሳምንት ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ምርምራ ከተደረገላቸው 380 ሰዎች ውስጥ 125 ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተገለጸ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የጤና ቢሮ ኃላፊዋ…

ኦነግ ያስገባውን ሰነድ ተከትሎ ቦርዱ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ያስገባውን ሰነድ ተከትሎ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡ ኦነግ በአቶ አራርሶ ቢቂላ በተጻፈ ደብዳቤ ሁለተኛውን ጠቅላላ ጉባዔ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ማካሄዱን በሰነዱ…

የሠራዊት አመራሮች ሀብት የማሣወቅ እና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራዊት አመራሮች ሀብት የማሣወቅ እና የመመዝገብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የመከላከያ ሥነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት አስታወቀ፡፡ የዳይሬክቶሬቱ ተወካይ ሌተናል ኮሎኔል ሀይሉ አሠፋ ዳይሬክቶሬቱ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን የሠራዊት አመራሮች…

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 5ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በሚያካሂደው 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድና በወቅታዊ ሃገራዊ ጉዳዮች…

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አንድ ጨዋታ እየቀረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡ በ17ኛው ሳምንት የሊጉ ውድድር አዳማ ከተማን 2 ለ 1 መርታቱን ተከትሎ ነው ሻምፒዮናነቱን ያረጋገጠው፡፡ በውድድር…

ፕሬዚዳንት ጆን ማጉፉሊ ሙስናን ለመከላከልና ጠንካራ የስራ ባሕል ለማዳበር ብርቱ ጥረት አድርገዋል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ሙስናን በመከላከል ጠንካራ የስራ ባህል እንዲዳብር ብርቱ ጥረት ማድረጋቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን አዲስ…

ዓለም እየተጋፈጠች ለምትገኘው ችግር ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች አስፈላጊዎች ናቸው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዓለም እየተጋፈጠች ለምትኝ ችግር ፈጠራ የታከለባቸው ምላሾች አስፈላጊዎች መሆናቸውን ተናገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የገንዘብ፣ እቅድ እና ኢኮኖሚ…

በኢትዮጵያ በቲቢ ምክንያት በየቀኑ 57 ሰዎች ይሞታሉ – የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር በቲቢ በሽታ ምክንያት በኢትዮጵያ በየቀኑ 57 ሰዎች እንደሚሞቱ አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቲቢ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤቶች የታዩ ቢሆንም አሁንም ትኩረት የሚሹ ችግሮች መኖራቸውን…