አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኮማንድ ፖስቱ ገደብ ተጥሎ በነበሩባቸው ሶስት ጉዳዮች ላይ ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም ፡-
1- የህዝብ ትራንስፖርት ከዛሬ በኋላ ያለ ሰዓት ገደብ እንዲንቀሳቀሱ ተፈቅዷል፤
2- ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የከተማ ታክሲዎች ገደብ ሁለት ስዓት ተጥሎባ የነበረ ቢሆንም ከዛሬ ጀምሮ ከዚህ ቀደም እንደነበረው መደበኛ አሰራር መሰረት እንዲንቀሳቀሱ እገዳው ተነስቷል፤
3- ታርጋ ያላቸው ሞተር ሳይክሎች ብቻ እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት ድረስ መንቀሳቀስ እንደሚቻል፣ አንድ ሰው ጭኖ መንቀሳቀስም አንዲችሉ መወሰኑን እንዲሁም ከአጎራባች ወደ ክልሉ የሚገቡ ሞተር ሳይክሎች እስከ 12 ሰዓት ድረስ ተጥሎ የነበረው እገዳ እስከ ምሽቱ አንድ ሰዓት ድረስ ተፈቅዷል፡፡
በሌላ መልኩ ማንኛውም ዜጋ የጦር መሳሪያዎቻቸውን እንዲያስመዘግቡ መልዕክት ተላልፎ የነበረ ሲሆን ÷ የጊዜ ገደቡ የተጠናቀቀ መሆኑንና ለማንኛውም ግለሰብ የጦር መሳሪያ ፍቃድ እንደማይሰጥ ተናግረዋል፡፡
ማሻሻያ ለማድረግ ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታ ለውጥ እያሳየ በመምጣቱ፣ የጠላት አቅምም እየተዳከመ መሆኑ እንዲሁም ዜጎች አካባቢያቸውን ነቅተው እየጠበቁ መገኘታቸውን ተከትሎ ለፀጥታ ስጋት በሚል የጣልናቸውን ክልከላዎች እንድናነሳ አድርጎናል ብለዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!