Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ-20 እና ዜድ ፍሊፕ የተሰኙ አዳዲስ ስልኮች ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) ግዙፉ የኤሌክትሮኒክስ አምራች ኩባንያ ሳምሰንግ  የ5ኛ ትውልድ (5 ጂ) ኢንተርኔት የሚጠቀሙ ጋላክሲ ኤስ-20 እና ዜድ ፍሊፕ የተሰኙ አዳዲስ ስልኮች ማምረቱን አስታውቋል።

አዲሱ ጋላክሲ ኤስ-20 ዘመናዊ ስልክ ምስሎችን በ100 እጥፍ የማጉላት አቅም ያለው ካሜራ የተገጠመለት መሆኑ ተመላክቷል።

ጋላክሲ ዜድ ፍሊፕ የተሰኘው ሁለተኛው ስልክ ደግሞ የመተጣጠፍ ችሎታ ያለው መሆኑን  ኩባንያው ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ቆሻሻዎችን እና የአቧራ ብናኞችን ማስወገድ የሚያስችሉ ጥቃቅን ቡርሾች ያሉት መሆኑ ተጠቁሟል።

በአሜሪካ 1ሺህ 380 ዶላር እና በብሪታኒያ 1ሺህ 300 ዩሮ የመሸጫ ዋጋ የተቆረጠለት ይህ ስልክ ከሁለት ቀናት በኋላ ለገበያ ይቀርባል ተብሏል።

ሳምሰንግ  የዓለማችን ዘመናዊ ስልኮች ግብይት ከሚፈጸምባት ቻይና ባሻገር  ወደ ሌሎች ሀገራት የሚያሰራጭ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በግብይት ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረበት መሆኑ ነው የተገለጸው።

ችግሩ በገበያው ላይ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመቋቋምም ኩባንያው የተለያዩ  ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑ ተመላክቷል።

ምንጭ ፥ ቢቢሲ

Exit mobile version