Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደቡብ ምእራብ ህዝቦች ክልል ከአንድ በላይ ማዕከላት ይኖረዋል – የክልሉ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛውን እና አዲሱን የደቡብ ምእራብ ህዝቦች ክልል ለመመስረት ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የክልሉ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶክተር ኢኒጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለፁ።

ሰብሳቢው ዛሬ በሰጡት መግለጫ ለአመታት በተለያየ ደረጃ ሲቀርብ የነበረ ጥያቄ መሆኑን አንስተው፥ ጥያቄው መልስ ያገኘው በለውጡ መንግስት መሆኑን ተናግረዋል።

ጥያቄው በርግጥም የህዝብ ለመሆኑ ለማረጋገጥ የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን እና ውይይቶች መካሄዳቸውን ገልፀዋል።

በፌደሬሽን ምክር ቤት እና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የህዝበ ውሳኔ ተደራጅቶ ውጤቱ 98 በመቶ ሆኖ የህዝብ ፍላጎት መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላም፥ ከክልሉ ረቂቅ ህገመንግስት ፣ መሪ የልማት እቅድ፣ ከቋንቋ ፣ አርማ፣ ማዕከላት እንዲሁም ሰንደቅ አላማ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ላይ ምክክር መካሄዱን ገልፀዋል።

አሁን ላይም የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ክልሉ ነገ በይፋ ይመሰረታል ነው ያሉት ሰብሳቢው።

ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ የህዝብን ጥያቄ ከግምት በማስገባት ከአንድ በላይ የሆኑ እኩል እውቅና ያላቸው ርእሰ ከተሞች ይኖራሉም ብለዋል።

ፍትሃዊ የመንግስትና የፖለቲካ ስልጣን እኩል ክፍፍል እንዲኖርም በህግ ማዕቀፉ ለማካተት ተሞክሯል ነው ያሉት።

በሃብታሙ ተክለስላሴ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version