የሀገር ውስጥ ዜና

ሁለት ታዳጊዎችን አግቶ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ የ25 ዓመት እስር ተፈረደበት

By Tibebu Kebede

February 12, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ የ7 ዓመት ህፃንና የ17 አመት ታዳጊን ከብት በመጠበቅ ላይ እያሉ አግቶ ገንዘብ የጠየቀው ግለሰብ የ25 ዓመት እስር ተበየነበት።

አገሬ የሗላሸት የተባለው ተከሳሽ፥ ሁናቸው ማስረሻ የተባለን የ17 ዓመት ታዳጊ ጳጉሜን 4 ቀን 2011 ዓ.ም አዴት ቀበሌ ከብት በመጠበቅ ላይ እያለ ካገተው በኋላ 30 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 20 ሺህ ብር መቀበሉ በክሱ ተመልክቷል።