Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ብቻ በ27 አለማቀፍ ከተሞች ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ አደረጉ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአለማቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያውያን በ27 ከተሞች የአሜሪካ መንግስት እና አንዳንድ የምእራባዊያንን መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉ ያሉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና የሚቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

ከደቡብ አፍሪካ እስከ ዋሽንግተን ዲሲ ነጩ ቤተ መንግስት በርካቶች የተሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል።

የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን የሀሰት ዘገባ እና መንግስታት በምርጫ ወደ ስልጣን የመጣ የኢትዮጵያን መንግስት በሀይል ለመጣል የሚያደርጉትን ጥረት ክፉኛ ኮንነዋል።

ሰልፈኞቹ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ በተለይም የአፍሪካ ቀንድ ህዝቦችን በመከፋፈል ላይ የተመሰረተ ፖሊሲዋን እንድታርም ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያን እጅ ለመጠመዘዝ የሚደረግ ሙከራ የአፍሪካን ነጻነት መግፈፊያ ዳግም የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲ አካል በመሆኑ “#NoMore” በቃ በሚለው መሪ መፈክራቸው ተቀባይነት እንደሌለው አስገንዝበዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ በርካቶች በተካፈሉበት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የኢትዮጵያን የአፍሪካ የነጻነት አርማነቷን፣ ወራሪዎችን አሳፍራ የመለሰች የጀግኖች አገር መሆኗን ፣ከጥቁር ህዝቦች በብቸኝነት በቅኝ አገዛዝ ጥላ ስር ያልወደቀች አገር መሆኗን በማስታወስ አሜሪካ የተሳሳተ ፖሊሲዋን ከማራመድ እንድትቆጠብ ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የህወሓት የሽብር ቡድንን መደገፍ የአፍሪካ ቀንድን እና መላ አህጉሪቱን አደጋ ላይ የሚጥል አካሄድ መሆኑን የፕሬዚደንት ባይደን አስተዳደር እንዲገነዘብ ሰልፈኞቹ ጠይቀዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

Exit mobile version