Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቱርክ በኢድሊብ 51 የሶሪያ ወታደሮች መገደላቸውን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ቱርክ በትናንትናው እለት በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ 51 የመንግስት ወታደሮች መገደላቸውን አስታወቀች።

ወታደሮቹ በኢድሊብ ግዛት በቱርክ የሚደገፉ ታጣቂዎች በወሰዱት እርምጃ መገደላቸውንም አንካራ ገልጻለች።

ከሞቱት ወታደሮች በተጨማሪም ሁለት የሶሪያ ታንኮች እና አንድ የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘን መውደማቸውን የቱርክ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሶሪያ ጦር በበኩሉ ከቱርክ ለተቃጣበት ጥቃት አፀፋዊ ምላሽ እሰጣለሁ ብሏል።

የሶሪያ ወታደሮች ከሳምንታት በፊት አሌፖን ከዋና ከተማዋ ደማስቆ ጋር የሚያገናኘውን ዋና መንገድ ከፈረንጆቹ 2012 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቆጣጥረዋል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም የሶሪያ አማጽያን እና የቱርክ ወታደሮች በሶሪያ ጦር ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

Exit mobile version