አዲስ አበባ፣ ህዳር 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ህዝብ በኢትዮጵያዊነቱና በማንነቱ ለመጣ ወራሪ ኃይል ምህረት እንደሌለው በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል ዘርፍ ኃላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ተናገሩ።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋርና በአማራ ክልሎች የፈጸመው ወረራም ኢትዮጵያውያንን ለዳግም ጭቆና የመዳረግ ጽኑ ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ መሆኑንም ገልጸዋል።
አሸባረው የህወሃት ወራሪ ኃይል ገብቶ በነበረባቸው የአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በርካታ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመቶችን አድርሷል።
ከ2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ጠቀሜታ ያላቸውን የህዝብ ንብረቶችን አውድሟል።
የሽብር ቡድኑ እንደ ግመል፣ ፍየል እና የመሳሰሉ የቁም እንስሳትን ጭምር በመግደል በአፋር ወገኖች ላይ የጭካኔ በትሩን አሳርፏል።
በንጹኃን ላይ የተፈጸመው አስነዋሪ ድርጊትም የአሸባሪውን የህወሃት ቡድን ሰይጣናዊ ምግባር የገለጠ ድርጊት ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል።
በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ማዕከል ዘርፍ ኃላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፥ አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአፋርና በአማራ ክልሎች የፈጸመው ወረራ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የመዳፈር ድርጊት ነው ብለዋል።
የሽብር ቡድኑን አስነዋሪ ወረራ ለመቀልበስም የአፋርና የአማራ ህዝቦች ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን እየቀለበሱት እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በአፋር ክልል በገባባቸው አካባቢዎች በርካታ ውድመቶች ያደረሰውን የሽብር ኃይል ለማጥፋትም የአፋር ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ከመካላከያ ሰራዊት ጋር በቅንጅት ውጤታማ ስራ እያከናወኑ መሆኑን ጠቁመዋል።
የአፋር ህዝብ በሽብር ቡድኑ የመግለጫ ጋጋታ፣ ፉከራ እና ንቀት የተሞላበት ንግግር እንደማይበገር ገልጸዋል።
የተፈጸመበትን ወረራና ግፍ በመቀልበስም በኢትዮጵያዊነቱና በማንነቱ ላይ የመጣን ኃይል በመቅበር ለጠላቱ ምህረት የሌለው ህዝብ መሆኑን እያስመሰከረ ነው ብለዋል።
በክልሉ ፕሬዚደንት ሃጂ አወል አርባ የሚመራው ኮማንድ ፖስት ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ውጤታማ ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
ቀደም ሲል የሽብር ቡድኑ አርብቶ አደሩ የአብዮታዊ ዴሞክራሲን መስፈርት አያሟላም በሚል ተልካሻ ምክንያት አጋር የሚል ስያሜ በመስጠት ለራሳቸው አገዛዝ የሚመች መዋቅር ሰርተው ሲበዘብዙ መቆየታቸውን አመላክተዋል።
የአፋር ህዝብም ሲደርስበት ከነበረው ጫና እና ጉስቁልና ተላቆ እንደሌሎቹ ሁሉ እራሱን በራሱ በማስተዳደር የአገርን ሉዓላዊነት በማስከበር በድል ጉዞ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪው የህወሃት ቡድን በአገር ሉዓላዊነት ላይ የደቀነው ፈተና በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ ኢትዮጵያውያን የጀመሩትን ተነሳሽነት በማስቀጠል ለግብዓተ መሬቱ የመፋጠን የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በሽብር ቡድኑ ምክንያት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ለተዳረጉ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!