Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እናቋርጠው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠው እጠይቃለሁ ሲሉ ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አሳሰቡ።
 
ጠ/ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ለኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት፥ ሀገሪቱ ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሥጋቶችን ስትጋፈጥ ብዙ ትግሎች እና ምቾት ማጣት ይኖርብናል ብለዋል።
 
ሁላችንም ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ይህንን ጊዜያዊ ማዕበል ከፍለን በአንድነት እንድናቋርጠውም ጠይቀዋል።
 
በአንድነት ከቆምን ማሸነፋችን ሰበር ዜና አይሆንም! ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ማሸነፍን ከዚህ በፊት አድርገነዋልና አሁንም እናደርገዋለን ብለዋል።
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
Exit mobile version