Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአሰላ ከተማ  መከላከያ ሰራዊቱን መደገፍ ዓላማው ያደረገ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሰላ ከተማ የአገር ሰላም ማስከበርን እና መከላከያ ሰራዊቱን መደገፍ ዓላማው ያደረገ ውይይት ከነጋዴው ማህበረሰብ ጋር እየተደረገ ነው።

በከተማው የሚገኙ ደረጃ ሀ እና ደረጃ ለ ነጋዴዎችን ባሳተፈው በዚህ ውይይት ላይ ፥ የአገርን ሉዓላዊነት  ለማስከበር እየተካሄደ ውየህልውና ዘመቻ እና  እየተዋደቀ ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊት  እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገልጿል።

የውይይቱ ተሳታፊ  ነጋዴዎችም  መከላከያ ሰራዊቱን እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት መቶ አለቃ ገበየሁ፥ በኢትዮ ሱማሌ ጦርነት ላይ መሳተፋቸውን አንስተዉ ፥”ዛሬ እዚህ ቆሜ መደፈራችን ያንገበግበኛል፣ ገንዘብ ሰጥቼ ብቻ መቅረትን አልፈልግም፣ ግንባር ድረስ ሄጄ ሀገሬን አስከብራለሁ” ብለዋል።

የአሰላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ  አቶ ገዛሊ አሹ በበኩላቸው ፥አሸባሪዎቹ የህወሓት እና የኦነግ ሸኔ ቡድኖች የውጭ ጠላቶችን አላማ ማስፈፀሚያ የክህደት ፈፃሚ ሆነዋል ብለዋል።

በመሆኑም ይህን ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ መከላከያውን መደገፍ እና ማገዝ የህልውና ግዴታ ነው ብለዋል።

አቅም ያለው ለህይወት መስዋዕትነት ግንባር ተመዋል ፣ግንባር ለመሄድ ያልቻልን ደግሞ በገንዘባችንን እንደግፍ ሀብት ሀገር ሰላም ካልሆነች የሚቀጥል አይደለምና ካለን ሀብት  ላይ እናጋራ  ብለዋል።

የድጋፍ ማሰባሰቢያና የምክክር መድረኩ ለመከላከያ ሰራዊቱ በከተማው ደረጃ  30 ሚሊየን ብር ድጋፍ ለመሰብሰብ የታቀደው እቅድ ማስፈጸሚያ መርሀ ግብር አንዱ አካል መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

በሊያ ዱጉማ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version