Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኦቢኤን ለመከላከያ ሰራዊት እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦቢኤን በአፋር ግንባር ለሚገኘው የአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የእርድ እንስሳትና የምግብ ድጋፍ አደረገ።

በዚህም ለተፈናቃዮች 400 ኩንታል ስንዴ ሲለግስ ለሰራዊቱ ደግሞ 15 ሰንጋዎችን አበርክቷል።

በስፍራው በመገኘት ድጋፉን ያስረከቡት የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር ዝናቡ አስራት፤ መገናኛ ብዙሃን ትክክለኛ መረጃ ለሕዝብ ከማድረስ ባለፈ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

በቀጣይም ተቋሙ ትክክለኛ መረጃዎችን ለሕዝቡ እያደረሰ፣ ድጋፍ ማድረግ ባለበት ጊዜም ድጋፍ ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አረጋግጠዋል።

የመከለከያ ሰራዊትን ወክለው ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ እዝ ሎጂስቲክስ፣ ቀለብና ንብረት መምሪያ ኃላፊ ሻለቃ ጌታቸው አስማረ የኢትዮጵያ ሕዝብ ደጀንነቱንና እያስመሰከረ ቀጥሏል ብለዋል።

የአፋር ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ከሎኢታ፤ ኦቢኤን ላደረገው ድጋፍ በክልሉ ሕዝብና መንግስት ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version