አዲስ አበባ፣ ህዳር 10፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው ዙር የኮቪድ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ እንደምሠጥ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ።
ቢሮው ክትባቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።
ከዛሬ ጀምሮ ባሉ 10 ቀናት ውስጥ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሰዎችን ለመከተብ እቅድ መያዙን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ተናግረዋል።
በክልሉ ከሚገኙ ከተሞች ውስጥ እድሜያቸዉ 12 ዓመት ከሆናቸው ጀምሮ ክትባት እንደሚሰጥና የተቀሩት ከ18 ዓመት በላይ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች እንደሚሰጥ ነው የገለፁት።
እስከ ታህሳስ ወር ከክልሉ ህዝብ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሰዎችን ለመከተብ አቅደው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኙ አቶ እንዳሻዉ ተናግረዋል።
ከማረሚያ ተቋማት ጀምሮ የተለያዩ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሠራተኞች እንዲሁም ተፈናቃይ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ በልዩ ትኩረት ይሠራል ብለዋል።
ከዛሬ ጀምሮ የሚሰጠው የመጀመሪያ ዙር የኮቭድ ክትባት ዘመቻ እንዲሳካ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አቶ እንዳሻዉ አሳስበዋል።
እስካሁን በተደረገዉ ክትትል በክልሉ ደረጃ 700 ሺህ ሰዎች የተከተቡ ሲሆን፣ 15 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን እንዲሁም 238 በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከክልሉ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በታመነ አረጋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን