አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለህልውና ዘመቻው 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉም÷ የምግብ፣ የአልባሳትና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስን ያካተተ መሆኑን÷ ድጋፉን ለደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ያስረከቡት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ወይንሸት ኃይሌ ተናግረዋል፡፡
የተቃጣብን የህልውና ጥቃት በሃገር የመጣ በመሆኑ÷ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሃብት አሰባሳቢና ህዝብ ንቅናቄ ቡድን መሪ ዶ/ር ገዛኸኝ ነጋ÷ ርቀት ሳይገድበው ለህልውና ዘመቻው ጥሪ በቀዳሚነት ምላሽ የሰጠውን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲን አመስግነዋል።
በሳምራዊት የስጋት
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!