የሀገር ውስጥ ዜና

ከወሎ ተፈናቅለው በደብረ ብርሀን ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በህልውና ዘመቻ ላይ ተወያዩ

By Meseret Awoke

November 18, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል የርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ መስፍን አበጀ፥ የአማራ ህዝብ እየገጠመው ያለውን ፈተና ለመሻገር ከምን ጊዜው በላቀ ደረጃ አቅሙን አስየባብሮ መዝመትና ጠላቶቹን ድል ማድረግ ይኖርበታል ሲሉ ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የመወያያ ጽሁፍ ያቀረቡት የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህሩ ዶክተር ሻምበል የጉማስ ፥ በዚህ ወቅት መዝመት እና አምርሮ መፋለም እንደሚገባ አስረድተዋል።

የአማራ ህዝብ የመጣበት ጠላት ህዝብን እንደ ህዝብ መኖሪያ ለማሳጣት እና ለማዋረድ ያቀደ በመሆኑ የአማራ ህዝብ በጋራ መነሳት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የተቆጣ እና የተቆጨ አማራ ለዘራፊው እና ለተስፋፊው ቡድን አስተማሪ ርምጃ መውሰድ እንዳለበትም ጠቁመዋል።

“ጠላትማ ምንጊዜም ጠላት ነው ቀድሞ አደብ ማስያዝ አሾክሿኪውን ነው” በማለት የአያት ቅድመ አያቶችን ብሂል የጠቀሱት ዶር ሻምበል የጉማስ ፥ ብሂሉ የውስጥ ባንዳን አደብ ለማስያዝ ሁነኛ ማስተማሪያ መሆኑን አስረድተዋል። ለባንዳ እና ለወራሪ ያልተገዙ ጀግኖችን የታሪክ ወርሰን ተላብሰን በጋራ መታገል ላጋጠመን ፈተና ብቸኛው መውጫ መንገዳችን ነው፥ ጊዜው ደግሞ አሁን ነው ብለዋል ዶክተር ሻምበል።

በኤልያስ ሹምዬ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!