አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲኒየር ኮሎኔል ማክ ቶክ ፕሮግ የተመራ በአብዬ ግዛት የተሰማራው የተመድ ጊዜያዊ የፀጥታ ሃይል (ዩኒስፋ) ወታደራዊ ልዑክ በአብዬ የሚገኘውን የ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የግዳጅ ቀጠና ጎብኝቷል።
ጉብኝቱ ዋና ማዘዣ ጣቢያውን ጨምሮ የ4ኛ ኤፒሲ ሻምበልን ያካተተ ሲሆን ÷ በቦታው ሲደርሱም በሻለቃው አመራሮች አቀባበልና እና ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
እንደ ኮሎኔል ማክ ቶክ ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ታሪክ የረጅም ጊዜ ልምድ ያላት ሀገር እንደመሆኗ መጠን፥ ይህንን ልምዷን በሚገባ በመጠቀም በቀጠናው ማምጣት የማይቻል የሚመስለውን ሰላምና መረጋጋት በማምጣት የሚደነቅ ተግባር አከናውናለች ፤ እያከናወነችም ትገኛለች ብለዋል።
የ24ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃም ብዙ ፈተናና ውጣ ውረዶችን በማለፍ በሁለቱ ጎሳዎች መካከል ሰላም እንዲነግስ ማድረጋቸው በአካባቢው የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰላም ወጥተው መግባታቸውና በየመንገዱ እንደልብ ሲንቀሳቀሱ ማየታቸው ህያው ምስክር መሆኑን መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!