አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) በጋምቤላ ክልል የሽብርተኛው ህወሓት ተላላኪ የሆነውና ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር (ጋነግ) ብሎ የሚጠራው ድርጅት አባል የነበሩ 24 ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ።
ለአሸባሪው ህወሐትና ሸኔ ተላላኪ በሆነው ጋነግ የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በመታለል ከቡድኑ ጋር ተቀላቅለው የነበሩ ሰዎች የቡድኑ ዓላማ አገር ማፍረስ መሆኑን በመገንዘብ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጥተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ እንዳሉት፥ ቡድኑ ከአሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ጋር አገር የማፍረስ ሴራ ነድፎ መንቀሳቀሱን በመቃወም ወጣቶቹ በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል።
በከሰረው በህወሓት ጁንታና በሸኔ ቡድን የሀሰት ትርክት ተሳስተው ጫካ ገብተው እንደነበም ነው የገለጹት፡፡
ቀሪ ያልተመለሱ የሽፍታው ቡድን አባላትም የመረጡት አማራጭ ስህተት እንደሆነ ተገንዝበው እጃቸውን በመስጠት በክልሉ ውስጥ በሚደረገው የሠላም እና የልማት እንቅስቃሴ ሚናቸውን መጫወት አለባቸው ብለዋል፡፡
የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የተመለሱ የቡድኑ ታጣቂዎች በበኩላቸው፥በተደረገላቸው አቀባበል መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ከትጥቅ ትግል ይልቅ ሠላማዊ መንገድ መከተል ለሁሉም አስፈላጊ መሆኑን መናገራቸውንም ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!