አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል አምስት ማዕከላት ያሉት ኮማንድ ፖስት አቋቁሞ ስራ መጀመሩን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊና የኮማንድ ፖስቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ ተናግርዋል።
ሀዋሳ ፣ለኩ፣ ይርጋለም ፣አለታ ጩኮ ና በንሳ ከተሞችን ማዕከላት ባደረገው ኮማንድ ፖስት በአንድ ሳምንት ውስጥ 83 ግለሰቦች ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ሆነዋል።
በተጨማሪም በአለታ ጬኮ በአንድ ግለሰብ ቤት 13 ሽጉጦችና የተለያዩ ጥይቶች ፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች ደግሞ የፖሊስና የመከላከያ አልባሳትን ጨምሮ 13 የባንክ ደብተሮች መያዛቸዉን አቶ አለማየሁ ገልፀዋል።
የክልሉ ኮማንድ ፖስት ከነገ ጀምሮ ገደብ የተጣለባቸውን እንቅስቃሴዎችና ክልከላዎችን ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት ፦
ባለሁለት እግር ተሽከርካሪ ሞተር ሳይክል (ታርጋ ያለው ብቻ) አንድ ሰው ጭኖ ከጠዋት 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ÷ ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ከጎንና ጎን ያለበሱትን ሸራ በማንሳትና ሶስት ሰው ብቻ በመጫን እስከ ምሽት ሁለት ሰዓት ፣ የህዝብ ትራንስፖርትና ታክሲዎች ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል ።
መታወቂያን በተመለከተም ÷ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ያሉ ሀላፊዎች መታወቂያ መስጠት የማይችሉና ማንነቱን የሚገልፅ መረጃ በመያዝ ግለሰቦች ከዛሬ ጀምሮ ጊዜያዊ መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ።
ከጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘም ÷ ከዚህ ቀደም ያስመዘገበም ያላስመዘገበም ከነገ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት በአቅራቢያው በሚገኙ የፖሊስ ተቋማት ማስመዝገብና የፈቃድ ወረቀት መያዝ ይኖርበታል።
ይህን ያላደረገና ያልተመዘገበ የጦር መሳሪያ ይዞ የተገኘ ማንኛውም አካል እንደ ወንጀለኛ የሚጠየቅ ይሆናል።
የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ሀላፊና የኮማንድ ፖስቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ እንደገለጹት ÷ ፋብሪካዎች፣ ኢንደስትሪ ፖርኮች፣ ሪዞርቶችና አለም አቀፍ ሆቴሎች የሰራተኛ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ከፖሊስ ኮሚሽኑ ፈቃድ ማግኘት ይችላሉ።
ከሲዳማ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ወደ ክልሉ የሚገቡ ባለሁለት እግር ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መግባት አይችሉም ያለው የክልሉ ኮማንድ ፖስት በእግረኞችና የቤት መኪኖች ላይ የሰዓት ገደብ ባይጣልም መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ያዛል ብለዋል።
በመቅደስ አስፋዉ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!