Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

95 ማራቶን በ 95 ቀን የሮጠችው ሴት በጊነስ የክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ሰፈረች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 95 ማራቶን ርቀት በ95 ቀን የሮጠችው ሴት በጊነስ የክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ስሟን ማስፈሯ አስገራሚ ሆኗል፡፡

አሊሳ ክላርክ ትባላለች ፤ እንስቷ በየቀኑ የአንድ ማራቶን ርቀት በመሮጥ እና ለ95 ቀናት ተመሳሳይ ርቀቱን በመሸፈኗ “95 የማራቶን ርቀት ሩጫ በ 95 ቀናት የሸፈነች እንስት በሚል” ስሟ በዓለም የጊነስ ክብረ ወሰን መዝገብ ላይ ሊሰፍር ችሏል፡፡

አጋጣሚው የተፈጠረው ፣ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ በጣሊያን ተባብሶ በነበረበት ወቅት የእንቅስቃሴ ገደብ በመጣሉ እና ተመዝግባ የነበረው የክረምት ማራቶን ውድድርም በመሰረዙ ምክንያት እልህ በመጋባቷ ነው ይላል ዘገባው፡፡

ባለፈው የፈረንጆቹ መጋቢት ወር በጣሊያን በርሊንግተን ትኖር የነበረችው አሊሳ ክላርክ ታዲያ ውድድሩ ቢቀርም እርቀቱን በየቀኑ ለ95 ቀናት ሮጣ ለመሸፈንና በጊነስ የዓለም ክብረወሰን መዝገብ ላይ ለመስፈር አላገዳትም ሲል የዘገበው ዩፒአይ ነው፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version