አዲስ አበባ፣ህዳር 7፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ከተለያዩ ዞኖችና አካባቢዎች የተውጣጡ የቀድሞ ሰራዊት አባላት ፣ ተመላሽ የሰራዊት አባላትና ሚሊሻዎች በዛሬው ዕለት በግንባር መከላከያ ሰራዊትን ተቀላቅለዋል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው አባላቱ እንደገለጹት÷ አገር ሳትኖር እንቅልፍ የለም፤ መተኛትም አይታሰብም።
አባላቱ ጁንታውና ተላላኪዎቹ በተለያዩ አካባቢዎች የፈፀሟቸው እንዲሁም እየፈፀሟቸው ያሉትን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን አውግዘዋል።
የሽብር ቡድኑን እና ወራሪውን ህወሓት የህይወት መስዋዕትነት ከፍሎ ለመቅበር መከላከያ ሰራዊትን በግንባር መቀላቀላቸውን ተናግረዋል።
የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የሚሊሻ ስምሪት ዳይሬክተር አቶ መርዕድ ዲዳ በበኩላቸው÷ የቀድሞ የሰራዊት አባላት የሀገርን ጥሪ ተቀብለው በሙሉ ፍቃደኝነት ወደ ግንባር መግባታቸውን አንስተዋል፡፡
የሰራዊት አባላቱ ከምንጊዜውም በላይ ጁንታውንና ጋላቢዎቹን ከኢትዮጵያ ለማጥፋት ቁርጠኛ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
በብስራት መንግስቱ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!