Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የምዕራባውያንን ጫና በጋራ መከላከል ይገባል – የዳያስፖራ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መሐመድ እንድሪስ÷ በኢስታንቡል በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስተባባሪነት በቱርክ የሚገኘው የአፍሪካ የትብብርና የትምህርት ማዕከል ባዘጋጀው መድረክ ለሚዲያ እና ቲንክ ታንክ ኃላፊዎች ገለፃ አድርገዋል።
በወቅቱም በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ የሚዲያና የምርምር ተቋማት ሊረዱት ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች አቅርበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ግጭቱ በአጭር ጊዜ ሊፈታ የሚችልበት እና የቀጠናው ሠላምን አስመልክቶ በርካታ ጉዳዮች አንስተዋል፡፡
ዶ/ር መሐመድ በማብራሪያቸው÷ ኢትዮጵያ አሁን የገጠማትን ችግር በውስጥ አቅሟ እና በወዳጅ ሀገራት በጎ ትብብር እንደምትወጣው ጠቁመው÷ የምዕራቡ አለም በሌሎች ሀገራት ላይ የሚያሳድሩትን ጫና በጋራ መከላከል እንደሚያስፈልግ መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version