Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ፖሊስ ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ ለሽብር ተግባር ሊውሉ የነበሩ ቁሳቁስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ ከተማ ፖሊስ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ ለሽብር ተግባር ሊውል የነበረ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እጽን ጨምሮ የተለያዩ መታወቂያዎችና የባንክ ደብተሮችን መያዙን አስታወቀ፡፡
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኢንስፔክተር ደረጄ ኢታና÷ በግለሰቡ መኖሪያ ቤትና ሱቅ ውስጥ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ 200 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስምንት ማዳበሪያ አደንዛዥ እጽ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በግለሰቡ መኖሪያ ቤት የተለያዩ ጂፒኤሶች፣ የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ገንዘቦች፣ በርካታ የባንክ ደብተሮችና በተለያዩ የግለሰቦች ስም የተመዘገቡ የኢትዮጵያ፣ የደቡብ ሱዳን እና የአዲስ አበባ መታወቂያዎች መያዛቸውን አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ወቅትም ግለሰቡ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአሶሳ ከተማ ፖሊስ በከተማው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ለማድረግ ከህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ኢንስፔክተር ደረጄ÷ ህብረተሰቡ አካባቢውን በንቃት በመከታተል የተለየ ሁኔታ ሲመለከት ለፖሊስ በመጠቆም የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version