Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ፕሮጀክት በዚህ በጀት አመት ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ፕሮጀክት በቀን 86 ሺህ ሜትር ኪዮብ ውሃ የማምረት አቅም ያለው ሲሆን በዚህ በጀት አመት ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታወቀ።
የለገዳዲ ክፍል ሁለት ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ ፕሮጀክት የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትን ለማመቻቸት በከፍተኛ አመራሮች የመስክ ጉብኝት ተደርጓል።
ጉብኝቱን ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ፣ የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ እና ከየተቋማቱ የተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር መሆኑን የከአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version