Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል የልዩ ሃይል ምልምል ፖሊሶችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 4 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሌጅ ለዘጠነኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የልዩ ሃይል ምልምል ፖሊሶች እያስመረቀ ነው።
ኮሌጁ እያስመረቃቸው ያሉት የልዩ ሃይል ምልምል ፖሊሶች አሁን ላይ የተለያዩ ወታደራዊ ትርኢቶችን እያሳዩ ነው።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ እና የልዩ ሃይል ፖሊስ ዋና አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ ተገኝተዋል።
በተጨማሪም የገቢዎች ሚኒስትር እና በአማራ ክልል የህልውና ዘመቻው የስልጠና ማዕከላት አስተባባሪ አቶ ላቀ አያሌው እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች መታደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
አካባቢህን ጠብቅ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
Exit mobile version