አዲስ አበባ፣ህዳር 4፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተመድ ሰራተኞቼ ያለ አግባብ እየታሰሩብኝ ነው የሚለው ክስ ምሰረተ ቢስ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪ ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ።
ሀላፊዋ ከሲጂቲኤን አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞቼ እየታሰሩብኝ ነው ብሎ መንግስትን ይከሳል፤ የእርሶ ምላሽ ምንድንነው ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ፥ ለኢትዮጵያ አጋር ከሚባሉ ተቋማት አንዱ የተመድ ነው ያሉት ቢልለኔ ስዩም በአሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ ተጠርጣሪን ጠርተህ ታናግራለህ፣ትመረምራለህ ይህ ነው የተደረገው ሲሉ አብራርተዋል።
በተቋሙ ውስጥ የሚደነቅ ስራ የሚሰሩት እንዳሉ ሁሉ በአፍራሽ ተግባር ውስጥ በመሳተፍ የአሸባሪው ህውሃትን ተልዕኮ የሚያሰፍጽሙ ተገኝተዋል ያሉት ቢልለኔ ስዩም መንግስት የሀገርን ሰላም እና አንድነት ለአደጋ የሚያጋልጡትን አይታገስም ብለዋል።
የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚደንት እና በአፍሪካ ቀንድ የፍሪካ ህብረት ልዩ መልክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን መንግስት እንዴት ይመለከተዋል? ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ፥ የአፍሪካን ህብረት ጥረት፣ ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ የሚለው እና የህብረቱን ውሳኔ በሚገባ እናከብራለን ብለዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን