Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የደጀን ወረዳ ተማሪዎች ወደ ግንባር የዘመቱ የሚሊሻ ቤተሰቦችን ሰብል ሰበሰቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ተማሪዎች ለህልውና ዘመቻው ወደ ግንባር የዘመቱ የሚሊሻ አባላት ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
 
በመርሃ ግብሩ የተሳተፉት ተማሪዎች የአገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር ቤት ንብረታቸውን ትተው በህልውና ዘመቻው ግንባር የዘመቱ የሚሊሻ አባላትን ሰብል አስቀድሞ መሰብሰብ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
 
ተማሪ ወርቁ ቁሜ በበኩሉ የዘማች ቤተሰቦች በኢኮኖሚ እንዳይቸገሩና ዘማች ሚሊሻውም ወደ ኋላ እንዳያስብ በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ በመደራጀት ቅድሚያ አዝመራቸው ሊሰበስብ ይገባል ብለዋል፡፡
 
በቀጣይም ትምህርታችንን በማይነካብን መልኩ ለህልውና ዘመቻው ግንባር ለሚፋለሙ የሚለሻ አባላት ድጋፋችንን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡
 
የዘማች ቤተሰቦች በበኩላቸው፥ ቤተሰቦቻቸው አገራቸውን ለማስከበር በህልውና ዘመቻው ቢሄዱም የአካባቢው ማህበረሰብና ተማሪዎች አዝመራውን በመሰብሰባቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
 
የአካባቢው መምህራኖችም ህብረተሰቡ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የአካባቢውን ሰላም ማስጠበቅ አለበት ማለታቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬስሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version