Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ምርታቸው ከደረጃ በታች በሆነ 9 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርታቸው ከደረጃ በታች በሆነ 9 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ መስፈርትን ያላሟሉ ምርቶችን ሲያመርቱ የተገኙ 9 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ነው ያስታወቀው።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለፉት 6 ወራት 210 ፋብሪካዎች ላይ ቁጥጥር ለማድረግ አቅዶ በ185 ድርጅቶች ላይ ቁጥጥርና ክትትል ማድረጉን ገልጿል፡፡

ቁጥጥር ከተደረገባቸው 185 ፋብሪካዎች ከ47 ፋብሪካዎች ወካይ ናሙናዎችን በመውሰድ የፊዚካል እና የላብራቶሪ ምርመራ አድርጓል።

በተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ ውጤት መሰረትም የ9 ፋብሪካዎች ምርት ከደረጃ በታች በመሆኑ ከማስጠንቀቂያ እስከ ማሸግ የሚደርስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

እርምጃ የተወሰደባቸው የሳሙና፣ የሲሚንቶ፣የውሃ እና የወይን ፋብሪካዎች ሲሆኑ÷ የ14 ፋብሪካዎች ናሙና የላብራቶሪ ውጤት እስከሚደርስ እየተጠበቀ መሆኑም ተገልጿል፡፡

162ቱ ፋብሪካዎች ደግሞ የኢትዮጵያን የጥራት ደረጃ መስፈርት ያሟሉ ሆነው መገኘታቸውን ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ከ90 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል ገለጸ፡፡

የዋጋ ንረትና የኑሮ ውድነት ለመከላከል በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚመራ ግብረ-ሀይል ከፌዴራል እስከ ወረዳ ድረስ ተዋቅሮ ሰፊ ስራ መሰራቴ ተጠቁሟል።

በዚህም በህገ-ወጥ መንገድ ግብይቱን ሲሳተፉ የነበሩ 91 ሺህ 602 ህገ-ወጥ ደላላዎችና ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ነው የተባለው።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version