የሀገር ውስጥ ዜና

የሃረሪ ጤና ቢሮ ለመከላከያ ሰራዊት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

By Feven Bishaw

November 12, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ግምቱ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የተለያየ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው÷ በአገር ላይ ከውጭ እና ከውስጥ የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት በክልሉ የተለያዩ የድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡