አዲስ አበባ፣ ህዳር 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ለመከላከያ ሰራዊት የሚሆን ግምቱ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የተለያየ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ተገኝተው÷ በአገር ላይ ከውጭ እና ከውስጥ የተቃጣውን ጦርነት ለመመከት በክልሉ የተለያዩ የድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ የጤና ባለሙያዎችም ሽኝት የተደረገላቸው ሲሆን÷ ሳንፈልግ ለገባንበት ጦርነት ሁሉም መመከትና የራሱን ድርሻ ማበርከት እንደሚገባ ነው የተገለጸው።
የጤና ባለሙያው ግንባር ድረስ በመዝለቅ ሰራዊቱን ለመደገፍ መነሳሳታቸው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ርእሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በክልሉ በስንቅ ዝግጅት፣ ወደ ግንባር በመዝመት፣ ደም በመለገስ እና በገንዘብ እየተከናወኑ የሚገኙት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ነው የተባለው።
የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኢብሳ ኢብራሂም በበኩላቸው÷ ግምቱ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል፡፡
ለሰራዊቱ የህክምና አገልግሎት የሚሰጡ 10 የጤና ባለሞያዎች ድሬደዋ በሚገኘው በምስራቅ እዝ ሪፈራል ሆስፒታል ተገኝተው የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ የተላኩ መሆናቸውን ጠቁመው በቀጣይ 41 የሚደርሱ የጤና ባለሙያዎች እስከ ግንባር ድረስ እንደሚላኩ ከሃረሪ ክልል ኮሚኒዩኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን