Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በመዲናዋ ብሔርን መሰረት ያደረገ ማዋከብ የለም – የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመዲናዋ ብሔርን መሰረት ያደረገ ማዋከብ እንዳለ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ገለጹ።

የመዲናዋ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የህልውና አደጋ በመቃወም ያካሄዱት ሰልፍ የዓለምን ትኩረት የሳበ እንደነበርም ተናግረዋል።

የ ‘ህወሃት’ እና ‘ሸኔ’ አሸባሪ ቡድኖችን አገር የማፍረስ ተልእኮ ለማስፈጸም እንደሚንቀሳቀስ የሚጠረጠር የየትኛውም ብሔር ተወላጅ በቁጥጥር ስር እንደሚውልም አስረድተዋል።

ዛሬ በሰጡት መግለጫ የከተማዋን ሰላም ለማረጋገጥ የጸጥታ አካላት ከህዝቡ ጋር በመሆን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ እየሰሩ ስለመሆኑ አንስተዋል።

በመዲናዋ የተጠርጣሪ ቤቶች ላይ የፍተሻ ስራ ከመጀመሩ በፊት የአዲስ አበባ የጸጥታ ቢሮ ፍቃድ ያላቸውም ሆነ ፍቃድ የሌላቸው የመሳሪያ ባለቤቶች እንዲያስመዘግቡ መደረጉንም ገልጸዋል።

አዲስ አበባ የበርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫና የፖለቲካ ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ሰላሟን ለማስጠበቅ የጸጥታ አካላት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰሩ ስለመሆኑም ጠቁመዋል።

በዚህም የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የሪፐብሊካን ጥበቃ እና የኦሮሚያ ፖሊስ በጋራ እየሰሩ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመዲናዋ በተደረገው የፍተሻ ስራ በቁጥር 27 ሺህ የሚሆን የትግራይ ልዩ ሃይል የደንብ ልብስ፣ የአፋር ልዩ ኃይል የደንብ ልብስ፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብሶች፣ የጦር ሜዳ መነጽሮች፣ ኮምፓስ፣ ሳተላይትና የጦር መሳሪዎች መገኘታቸውን አንስተዋል።

በተጨማሪ በርካታ የባንክ ደብተሮች፣ ፓስፖርቶችና የተለያዩ የውጭ ሀገራት የብር ኖቶች መገኘታቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

የጸጥታ አካላት የመዲናዋን ሰላም ለመጠበቅ እያከናወኑ ያሉትን ፍተሻና ተጠርጣሪዎችን የመያዝ ተግባር ከብሔርና ማንነት ጋር ለማያያዝ የሚጥሩ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው ይህም ከእውነት የራቀ አሉባልታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የመዲናዋ ነዋሪዎች ሀገርን ለማደን ለቀረበው ጥሪ እየሰጡት ላለው ምላሽ ምስጋናም አቅርበዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version