የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ አከራዮች የተከራዩን መሉ መረጃ እንዲያስመዘግቡ ፖሊስ አሳሰበ

By Meseret Awoke

November 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት አከራዮች የተከራዩን መሉ መረጃ እንዲያስመዘግቡ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

በከተማዋ ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎችና በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች የተከራዩን መሉ መረጃ በመያዝ በግንባር በመቅረብ እንዲያስመዘግብ ነው ፖሊስ መልእክቱን ያስተላለፈው፡፡

የፀጥታ ኃይሉ ለህብረተሰቡ ስጋት የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ የገለጸው ፖሊስ፥ እጅግ አበረታች ውጤት እየተመዘገበ ነው ብሏል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዝ የፀጥታ ሥራውን የሚደግፉ ልዩ ልዩ መመሪያዎችን ማውጣቱ ይታወቃል፡፡

በዚህ መሰረት ማንኛውም የመኖሪያ ቤት አከራይ መመሪያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተከራዩን ማንነት የሚገልፅ ማስረጃ በመያዝ እንዲያስመዘግብ ነው የተጠየቀው፡፡

መመሪያውን ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የከተማዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት እያደረገ ላለው ሙሉ ተባባሪነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን እያቀረበ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!