አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን የአፍሪካ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሁሪያ አሊ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ገለፁ፡፡
“በቴክኖሎጂ ሃያል ለመሆን የኢትዮጵያ ጉዞ” በሚል በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ሁሪያ አሊ ኢትዮጵያ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ወደ ፊት መራመድ እንድትችል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ለመድረኩ አብራርተዋል።
የቴሌኮም ዘርፍ ማሻሻያ፣ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ማስፋፊያ፣ የኤሌክትሮኒክስ ትራንዛክሽን አዋጅ፣ የጀማሪ ቴክኖሎጂ ድርጅቶች አዋጅ፣ የግል ዴታ ጥበቃ አዋጅ፣ የዲጂታል መታወቂያ፣ የስራ ቅልጥፍና እና የ ኢ-ክፍያ ስትራቴጂ የኢትዮጵያ መንግስት በትኩረት እየሰራባቸው ያሉ ስራዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ፓርኮችን መሰረተ ልማት ማሟላት፣ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን ማስፋፋት፣ የዲጂታል እውቀትን ማስፋት፣ የበይነ መረብ ደህንነትን ማስጠበቅ እና የሰው ሃይል ግንባታ ላይ ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።
በመድረኩ ከተለያዩ የፍሪካ አገራት የተውጣጡ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች አመራሮች፣ የቴክኖሎጁ የፋይናንስ ተቋማትና የባንክ ኃላፊዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!