አዲስ አበባ፣ ህዳር 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በየትኛውም አይነት ችግር ውስጥ ብታልፍም ልማት እና ብልፅግናዋን ከማረጋገጥ ወደ ኋላ እንደማትል የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ ተናገሩ፡፡
ሚኒስትሯ በዛሬው እለት በኢትዮጵያ የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤሊ አፕተን ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም በኢትዮጵያ እና በኒውዚላንድ መካከል የቆየው የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመን የጀመረ መሆኑን በማስታወስ÷ ሀገራቱ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ ማለትም በግብርና፣ በቢዝነስ እና በምርምር ስራዎች ላይ የዳበረ ግንኙነት እንደነበራቸው ገልፀዋል።
በዚህ ፈታኝ ወቅት በኢኮኖሚው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው እድገት ከፍተኛ መንግስት ለልማት ያለውን ቁርጠኛ አቋም የሚያመለክት መሆኑን ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ በቀጣይም በየትኛውም አይነት ችግር ውስጥ ብታልፍም ዕድገት፣ ልማት እና ብልፅግናዋን ከማረጋገጥ ወደ ኋላ እንደማትል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
የኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤሊ ኡፕተን በበኩላቸው÷ አገራቸው የኢትዮጵያ የልማት አጋር መሆኗን በመጥቀስ ሀገሪቱ ያለችበትን ከባድ ወቅት እንድታልፍ መንግሥታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በትብብር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
ሁለቱ አገራት በቀጣይ በግብርና፣ ግብርና ማቀነባበር፣ በኢንዱስትሪ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ፣ በምርምር ዘርፍ እና በኢንቨስትመንት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ለመስራት መስማማታቸውን ከሚኒስቴሩ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም በቀጠናው የሚኖረውን የንግድ ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ከሚመለከታቸው ዓለም አቀፍ እንዲሁም አህጉራዊ ድርጅቶች ጋር በጋራ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡