Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በስልጤ ዞን ተከስቶ የነበረውን ዋግ ሳይስፋፋ መከላከል ተችሏል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 2 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በስልጤ ዞን ስልጢ ወረዳ በስንዴ ላይ ተከስቶ የነበረው ዋግ ሳይስፋፋ መከላከል መቻሉን የወረዳው እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ መሃመድ አህመዲን ዋግ በተከሰተበት 271 ሄክታር ማሳ ላይ የኬሚካል ርጭት በማድረግ በሽታው ሳይስፋፋ መከላከል መቻሉን ተናግረዋል።

የአርሶ አደሮች የማሳ አትክልትና ቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ በሽታው ሳይስፋፋ መከላከል እንዳስቻለም ነው የተናገሩት፡፡

የኬሚካል እጥረት መኖሩን ያነሱት አቶ መሃመድ ያለውን በማቻቻል ለአርሶአደሩ እንዲደርስ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡

ዋግ በተለያየ መልኩ ሰብል የሚጎዳ በሽታ እንደመሆኑ ማሳ መቃኘት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

 

በኤርሚያስ ቦጋለ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Exit mobile version