የሀገር ውስጥ ዜና

የጋምቤላ ክልል የመጃንግ ብሔርሰብ ዞን በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

November 10, 2021

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የጋምቤላ ክልል የማጃንግ ብሔርሰብ ዞን በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙና በጦርነት ምክንያት ከተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ በደብረብርሀን ከተማ በመገኘት አደረገ ።

የመጀንግ ብሔረሰብ ዞን አስተዳዳሪ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት ድጋፉ የመጀመሪያ አለመሆኑን ጠቁመዉ ÷ ተፈናቃዮቹ የግድ እንደሚያስፈልጋቸዉ ስላመንን በሁለት ሳምንት ዉሰጥ ከዞኑ ህዝብ መሰብሰቡን ገልፀዋል ።

ዋና አስተዳዳሪዉ አቶ አብረሐም ማይክል ÷ ከዚህ በኋላም በተከታታይ ችግሩ እስከሚፈታ ህዝቡ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ።

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገ/ፃዲቅ በአሁኑ ሰዓት በዞናቸዉ ከ218ሺህ በለይ በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች መኖራቸዉን ገልፀው ÷ የመጀንግ ዞንና ህዝብ ስላደረገዉ ድጋፍ አመስግነዋል::

በጋራ ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ እንለፈው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል ።

በዛሬዉ እለት የተደረገዉ ድጋፍ 733 ኩንታል በቆሎና ከ3ሺህ 200 በላይ አልባሳት በአጠቃላይ ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ድጋ መደረጉን ለማወቅ ተችሏል ።

በብስራት መንግስቱ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!