የሀገር ውስጥ ዜና

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን  የ12ኛ ክፍል ፈተና አሰጣጥ ሂደትን ጎበኙ

By Melaku Gedif

November 10, 2021

አዲስ አበባ፣  ህዳር 01፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)  የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የ12ኛ ክፍል ፈተና  ሂደትን  በፈተና ጣቢያዎች በመገኘት ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

በሀረሪ ክልል እየተሰጠ ያለውን የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከተጀመረበት ዕለት አንስቶ ያለምንም ችግር እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙክታር ሳሊህ በሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የፈተና አሰጣጡን ተዘዋውረው በተመለከቱበት ወቅት እንደገለጹት÷ ፈተናው በክልሉ በተቋቋሙ ሁለት የፈተና ጣቢያዎች ያለምንም ችግር እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ፈተናው ከመጀመሩ በፊት በተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አማካኝነት ችግር ሳያጋጥም ተማሪዎች ፈተናቸውን እየወሰዱ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ሙክታር÷ ተፈታኞችም ፈተናውን በተረጋጋና በተቀመጠውን የፈተና ደንብ አክብረው እየወሰዱ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪም በፈተና ጣቢያዎች በመገኘት የፈተና አሰጣጡን ተዘዋውረው  ጎብኝተዋል፡፡

በሀረሪ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን 1ሺህ 267 ተማሪዎች እየወሰዱ ሲሆን ÷በተያዘው መርሃ ግብርም ነገ ይጠናቀቃል፡፡

 

በተሾመ ኃይሉ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡