አዲስ አበባ ፣ ህዳር 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ወደ ውጪ ከተላከ የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙኒኬሽን ዕቃዎች 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡
የኤሌክትሪክ ኤሌክትሮኒክስና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ፀሀዬ ይነሱ፥ የማምረቻ ኢንዱስትሪውን የግብይት አቅም ለማሳደግ የምርትና የግብዓት ትስስር የመፍጠርና ቅንጅታዊ አሰራርን የማጎልበት ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።
ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በተሰሩ ስራዎች 4 ፕሮጀክቶች ወደ ማምረት የተሸጋገሩ ሲሆን ሶስት ኢንተር ፕራይዞች ደግሞ የማስፋፊያ ስራ መከናወኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።