Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከንቲባ አዳነች መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ ለቀረበው ጥሪ ምላሽ ለሰጡ አካላት ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መከላከያ ሠራዊትን ለመደገፍ በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቀረቡ፡፡
 
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ÷ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንን ለመደገፍ እና አሸባሪው ህወሃት በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ትናንት ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ባካሄድነው ኢትዮጵያን የማዳን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከ1 ቢሊየን 540 ሚሊየን ብር በላይ ማሰባሰብ ችለናል ብለዋል።
 
ድጋፉን ላደረጋችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ እወዳለሁ ሲሉም በፅሁፋቸው አስፍረዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version