የሀገር ውስጥ ዜና

በአዋጁ ትግበራ በተደረገ ክትትል 237 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Feven Bishaw

November 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ትግበራ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በተደረገ ጥብቅ ክትትል 237 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ነብዩ ኢሣያስ አሸባሪው ህወሓትና ሸኔ ሀገር በማፍረስ ሴራ መጠመዳቸውን ጠቅሰው÷ ቡድኖቹን ለመመከት ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።