Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በእንግሊዝ ተጨማሪ አራት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ተጨማሪ አራት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኙ።

ይህን ተከትሎም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ስምንት መድረሳቸውን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰወች በለይቶ ማቆያ ስፍራ ክትትል እያደረገላቸው መሆኑንም ገልጿል።

ዓለም ላይ ከ40 ሺህ በላይ የቫይረሱ ተጠቂወች እንደሚገኙ መረጃወች ያመላክታሉ።

በቻይና በቫይረሱ ሳቢያ እስካሁን 908 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ በየቀኑ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ግን መሻሻል እየታየበት መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Exit mobile version