አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ገንዘባችንና ህይወታችን ለህልውናችን” በሚል መሪ ሃሳብ የጎንደር ከተማ ባለሃብቶች ውይይት እያካሄዱ ነው።
ውይይቱን ያስጀመሩት የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ባለሃብቱ በእካሁኑ የህልውና ዘመቻ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል ነው ያሉት።
አሁንም “ጥይት ለጠላቴ ስነቅ ከወገኔ” ብለው የሄዱና መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፋችንን እናስቀጥል ለማለት ነው ብለዋል።
የጎንደር ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ለህልውና ዘመቻው ከባለሃብቱ ጋር እያካሄደ ባለው ውይይት በተለያዩ ዘርፍ የተሰማሩ ባለሃብቶች ለህልውና ዘመቻው ትናንት ድጋፍ አድርገናል፤ ዛሬም ነገም እንቀጥላለን ብለዋል።
ሃብት ማፍራት የሚቻለው ሃገር ሲኖር ነውና ኢትዮጵያ ሰላሟ እስኪረጋገጥ ከሃገር መከላከያ ከልዩ ኃይል ሚሊሻና ፋኖ ጎን ነን ብለዋል።
የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባና የሃብት አሰባሳቢ ግብረሃይል ሰብሳቢ አቶ ባዩ አቡሃይ ፥ እስካሁን በጥሬ ገንዘብ ከ69 ሚልየን በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን ገልጸው በስንቅም ከ54 ሚሊየን ብር በለይ የሚገመት ስንቅ ተሰባስቧል።
አሁንም የባለሃብቶቹ ፈቃደኝነት የሚያበረታታ ነው ብለዋል።
በሰላም አስመላሽ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!