አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአርሲ ዞን ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡ ነዋሪዎች የህወሀት እና ሸኔን ጥምረት በማውገዝ የተለያዩ መፈክሮችን በአሰላ አረንጎዴ ስታድየም አሰምተዋል።
ባለፉት 27 አመታት በግፉ አገዛዝ ስር የነበርን ዜጎች ነፃነታችንን ባወጅንበት ማግስት ዳግም የህወሀትን የስልጣን ጥሙን መታገስ አንችልም ብለዋል።
ከአርሲ ዞን እና አሰላ ከተማ የተወጣጡ በሺወች የሚቆጠሩ ዜጎች እኔም ለሀገሬ ወታደር ነኝ ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ በሚሉ መልዕክቶች ሰልፉ ላይ ታድመዋል።
ሸኔ ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ በሚል ትርክት ህልሙን ለማሳካት ከመሰሉ ጋር መጣመሩ የራዕይውን ሀሰትነት የሚያመሳክር እና ፍፁም ሽብርተኛ መሆኑን ያረጋገጠ ነዉ ብለዋል ።
ህዝቡ የጥቅምት 24፣2013 ቱን የሰሜን እዝ ጥቃት እና ጭፍጨፋ በማስታወስ ይህ ክስተት ለሀገራችን በአንድነት እንድንቆም እና ሰራዊቱን እንድንቀላቀል አድርጎናል ነዉ ያሉት።
የአሰላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ገዛሊ ሀሹ በበኩላቸዉ፥ የሽብር ቡድኖቹ ጥምረት እንደማይዘልቅ አንስተዉ ኢትየዮጲያ ታላቅ ሀገር ናት በአደዋ ድላችን አለምን ያነጋገርች በቀላሉም የማትፈርስ ነች ብለዋል።
የአርሲ ዞን ዋና አስተደዳደር አቶ ሙሳ ፊሮ እነኚህ አሸባሪ ቡድኖች ማንነታችንን ማወቅ ከፈለጉ ጣሊያንን ይጠይቁ ሲሉም ዜጎች በኢትዮጲያዊነታቸዉ እንደማይደራራደሩ ተናግረዋል።
በሊያ ዱጉማ
አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!