የሀገር ውስጥ ዜና

የአድዋ ልጆች መሆናችንን እረስተው በአጎዋ ሊያስፈራሩን ይሞክራሉ-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Feven Bishaw

November 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ ምዕራባውያን ሃገሮች የአድዋ ልጆች መሆናችንን እረስተው በአጉዋ ሊያስፈራሩን ይሞክራሉ ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ፡፡ ከንቲባዋ በመስቀን አደባባይ በተካሄደው አሸባሪዎቹን ህወሓት እና ሸኔን የሚያወግዝ ሰልፍ ላይ ተገኝተዋል፡፡