የሀገር ውስጥ ዜና

መንግስት አሸባሪዎቹን ህውሓትን እና ሸኔን ለማጥፋት የሚያደርገውን ጥረት እንደግፋለን – በኦሮሚያ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች

By Meseret Awoke

November 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት አሸባሪዎቹን ህውሓትን እና ሸኔን ለማጥፋት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፉና እስከ ህይወት መስዕዋትነት ድረስ የሚጠበቅባቸውን ለመክፈል ዝግጁ ነን ሲሉ በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ።

በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ፓርቲዎቹ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ተወያይተው በሰጡት መግለጫ ፥ በሰላም እና ጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከመንግስት ጋር ተባብረን እንሰራለን ነው ያሉት።

መንግስት፥ የአገር ህልውናን ለማጥፋት የተነሱትን አሸባሪዎቹን ህውሓትን እና ሸኔን ለማጥፋት በሚያደረገው ጥረት ውስጥ እስከ ህይወት መስዕዋትነት ድረስ የሚጠበቅብንን ለመክፈል ተዘጋጅተናል ብሏል።

በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉም ነው በጋራ መግለጫው ያመለከቱት።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ አባላትም፥ አሸባሪው ህወሓትና የእሱ ደጋፊ የሆኑ የተለያዩ ተቋማት ከሚያሰራጩት የሀሰት መረጃ እንዲታቀቡና በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተመስርተው በአገር ውስጥ ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም መያዝ እንደሌለባቸው ፓርቲዎቹ አሳስበዋል።

በደግማዊ ዴግሲሳ

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!