የሀገር ውስጥ ዜና

የዋርካዎች መሰብሰብ ደኑን የማይደፈር እያደረገው ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

By Meseret Awoke

November 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በዚህ ፈታኝ ጊዜ የኢትዮጵያ ልጆች ከጫፍ እስከጫፍ ተነስተዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ÷ የመጨረሻው ከባዱ ምጥ ልጁ የሚወለድበት ነው ፤ ይህ ፈታኝ ጊዜም ጀግኖች የሚወለዱበት ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች ከጫፍ እስከጫፍ ተነሥተዋል ፤ ፈተናዎቹ አጠንክረውናል ፤ ፈታኞቻችን ሌሎች መንገዶችን አሳይተውናል ሲሉ መልዕክታቸውን አጋርተዋል።

ፊታቸውን ካዞሩብን ወዳጆች እጥፍ የቁርጥ ቀን ወዳጆች አግኝተናልም ነው ያሉት።

የቅጠሎች መሰብሰብ ዋርካ አያደርጋቸውም ፤ የዋርካዎች መሰብሰብ ግን ደኑን የማይደፈር እያደረገው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ÷ የሚከፈል መሥዋዕትነት አለ ፤ ያ መሥዋዕትነት ግን ኢትዮጵያን ዋጅቶ በዐለት ላይ ይተክላታል ብለዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!